በኢትዮጵያ አሽከርካዎች ዳግም ተመዝነው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ያለው የትራንስፖርት ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ነው፡፡
የአሽከርካዎች ዳግም ምዘና ያስፈለገውም በአደጋ መበራከት ምክንያት ነው ብሏል፡፡
በመሆኑም የአሽከርካሪዎች ዳግም ምዘና ከተካሄደ በኋላ መንጃ ፈቃድ ብቻ ሳይሆን የሙያ ብቃት ማረጋገጫም ይዘው መገኘት ይጠበቅባቸዋል ብሏል ተቋሙ፡፡
በዚህ ዓመትም የሙያ ብቃት ምዘናው በህዝብና ደረቅ ጭነት እንዲሁም በፈሳሽ ጭነት አሽከርካሪዎች ይጀመራል ተብሏል፡፡
