“በመኾኒ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመው የዓመፅ ድርጊት፣ የተደራጀ የወንጀለኞች ኔትወርክ በትግራይ ህዝብ ላይ ሲፈጽመው የቆየውና በቀጣይነትም ሊፈጽመው የሚፈልገው የጭቆናና የጥፋት ማሳያ እንጂ!አንድ የተለየ ክስተት አይደለም።
በጣት ለሚቆጠሩ ኋላቀሮች ህልውና ሲባል የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ቢጠፋ እንኳን ቅንጣት ታህል ግድ የማይሰጠው ቡድን፤ በህዝባችን ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ጥፋት ማምጣቱ አይቀሬ ነው።
ምርጫችን፤ ሽፍቶቹ ህዝባችንን በክለው እንዲጠፉ መተው ነው ወይስ ለሞትና ስደት የዳረጉንን ሽፍቶች ማስወገድ? በሚለው ላይ የህዝቡ ህልውና የሚያሳስበው እያንዳንዱ ዜጋ ሊያስብበት የሚገባ ጉዳይ ነው።
በህይወት ዘመናቸው ሁሉ የውይይትና የሰላማዊ መፍትሄ ቋንቋ የማይገባቸው የሌብነትና የጭቆና መሐንዲሶች በሞታቸው አፋፍ ላይ ባህሪያቸውን ያሻሽላሉ ብሎ መጠበቅ ቂልነት ብቻ ነው።
ይበቃቸዋል!
ጌታቸው ረዳ በትግርኛ የፃፉት
