አንድ ኪሎ ቡና 220 ሺ ብር በመሸጥ ሪከርድ ሰበሩ

Date:


ቴስቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኀበር / ቴስቲ ኮፊ / በ ባለቤቱ “ፈይሰል አብዶሽ ሲግኔቸር ” በሚል  ያቀረበውና ተቀማጭነቱን  በእንግሊዝ እና አሜሪካ ባደረገው ኤም ካልቲቮዌብ ሳይት ባወጣው ኦንላይን የስፔሻሊቲ ቡና ጨረታ በኢትዮጵያ ከፍተኛውን ሽያጭ  ማለትም ለአንድ ኪሎ ግራም ቡና 1 ሺ 604  የአሜሪካን ዶላር  ወይንም 220 ሺ ብር ገደማ አስገኝቷል።

ሽያጩ በኢትዮጵያ ከፍተኛውን የቡና ዋጋ ያስመዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡናም በዓለም ገበያ ተፈላጊነቱ መጨመሩን ያሳያልም ተብሏል። ቴስቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኀበር በአቶ ፈይሰል አብዶሽ ባለቤትነትና ዋና ሥራ አስፈፃሚነት የሚመራ ሲኾን ትልቁ የኢትዮጵያ ቡና ሽያጭ ሪከርድ የተመዘገበበት ዓለም አቀፍ ጨረታ የተከናወነው ሀምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

ይህም ውጤት በቡና ኢንዱስትሪ ውስጥ ጉልህ የሆነ ምዕራፍ ነው። ጨረታው የደመቀ ተሳትፎ የታየበት ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ የሽያጭ ሪከርድ የተመዘገበበት  ስለመሆኑ  በድረ ገፁ ተመልክቷል።ከዚህ ጨረታ የተገኘው አጠቃላይ ገቢ 115 ሺ 286 ዶላር ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የሚውለው ቴስቲ ፋውንዴሽን ለአርሶአደሩ ማህበረሰብ በሻኪሶ ለሚያስገነባው ጤና ጣቢያ ግንባታ እንደሆነም ታውቋል።

ቴስቲ ኮፊ ከዚህ በፊት በተለያዩ የሀገራችን ከተማዎች በይርጋ ጨፌ፣ ሲዳማ፣ ምእራብ አሩሲ እና ሻኪሶ ለሚገኙ የአካባቢው ማህበረሰብ 5  ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ በማስረከብ ማኀበራዊ ኃላፊነት አበርክቷል። ቴስቲ ኮፊ ኩባንያ በአቶ ፈይሰል አብዶሽ  የተመሰረተው እኤአ  በ2009 ዓ.ም  ሲኾን በኢትዮጵያ ስመ ጥር ከሆኑ 10 ቀዳሚ ቡና ላኪ ኩባንያዎች አንዱ ነው። በዚህ ባሳለፍነው የ 2017 በጀት አመት በ 12 ወራት ውስጥ 52 ሚልዮን ዶላር ከኤክስፖርት የውጭ ምንዛሪ ለሀገራችን ያስገኘ ትልቅ ኩባንያ ነው።

ኩባንያው ቡና የሚልክባቸው ሀገራት ኮሪያ፣ ጃፓን፣  አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ታይዋን እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ናቸው። ኩባንያው ከ 30 በላይ የቡና ማጠቢያ እና ሳይቶች ያሉት ሲሆን የራሱ ቡና ማበጠሪያ፣ ማከማቻና ሮስቲንግ እንዳለው ብስራት ያገኘዉ መረጃ ያሳያል።ኩባንያው ስፔሻሊቲ ቡና አለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ ከላይ ወደተጠቀሱት አገሮች በመላክ ይታወቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...