በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በይፋ የተመሠረተው ፎረሙ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በብሔራዊ የልማት፣ ፈጠራና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተጠቁሟል።
በፎረሙ የሚካተቱ ተቋማት፦
🟠 በምርምር፣
🟠 በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም፣
🟠 በፋኩልቲ ልማት እና
🟠 የፈጠራ ማዕቀፎች ላይ የተሰማሩ እንዲሆኑ ይጠበቃል ነው የተባለው።
ፎረሙ የምርምር ላቦራቶሪዎችና ዲጂታል ፕላትፎርሞችን በጋራ መጠቀምና በእውቀት ሽግግርና በማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች ልምዶችንና አዳዲስ አሠራሮችን መለዋወጥ የሚያስችል መሆኑን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
