በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ ለሁለት አስርተ ዓመታት የዘለቀ ደማቅ አሻራ ያለው አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፤ ለጥበብ ባበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ እሁድ የካቲት 1 2018 ዓ.ም ምሽት ልዩ የክብር ሽልማት ተረክቧል።
ሽልማቱ የተሰጠው አርቲስቱ በሙያው ላይ ባሳየው ፅናት፣ ተከታታይነት ያለው ብቃት እና ለጥበብ ባለው ታማኝነት እንደሆነ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ሰለሞን ከችሎታው ባሻገር በመልካም ስነ-ምግባሩና በትህትናው የሚታወቅ የብዙዎች አርአያ ነው።
ሁልጊዜም በማንኛውም መድረክ “የቄራ ልጅ” መሆኑን በኩራት የሚናገረው ሰለሞን ቦጋለ፤ ታታሪነትና ትጋት ካለ ከየትኛውም የህይወት ደረጃ ተነስተው ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚቻል ለወጣቶች ህያው ምስክር ሆኗል።
በሽልማቱ ላይ የታደሙ የጥበብ ቤተሰቦች “ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ይገባል” በሚል የአርቲስቱን የዘመናት ድካም የካሰ ሽልማት መሆኑን በደስታ ገልጸዋል።
እንኳን ደስ አለህ!
እኛም ለኢትዮጵያ ፊልም እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከተው ለተወዳጁ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ “እንኳን ደስ አለህ” እንላለን።
ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ይገባል!
እንኳን ደስ አለህ ሰለሞን ቦጋለ!
የቄራ አካባቢ ማህበር
