የዓለምን ሰላም ለማምጣት የታለመና አንድ ሚሊዮን ሕፃናትን ያሳተፈ የሜዲቴሽን መርሃ ግብር በታይላንድ

Date:

በዓለማችን እጅግ አስገራሚ ከተባሉ መንፈሳዊ ትዕይንቶች መካከል አንዱ በታይላንድ መከናወኑ ተገልጿል። ከአምስት ሺህ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ አንድ ሚሊዮን ሕፃናት በአንድነት በመሰብሰብ ለዓለም ሰላም የህሊና ጸጥታ ወይም ሜዲቴሽን ማድረጋቸው ተነግሯል።

ይህ መጠነ ሰፊ መርሃ ግብር “ሰላም የሚጀምረው ከውስጥ ነው” የሚለውን መርህ መሠረት ያደረገ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ሕፃናቱ በጋራ በመሆን የሰላም፣ የፍቅር እና የረጋ መንፈስ ለዓለም እንዲሰራጭ አዎንታዊ ኃይልን እንደላኩም ተመላክቷል።

መርሃ ግብሩ ሕፃናቱ በዝምታ ውስጥ ሆነው አንድ ዓይነት ዓላማን በማንገብ፣ ሰላም በታላላቅ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ብቻ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ በሚደረግ የውስጥ ሰላም እንደሚመጣ ያስመሰከሩበት ነው ተብሏል።

ትንንሽ የሚመስሉ የሰላም እርምጃዎች እንደ ዝምታና ትንፋሽን የመቆጣጠር ልምምድ በዓለም ላይ ትልቅ ለውጥ የማምጣት አቅም እንዳላቸውም ትምህርት ተሰጥቶበታል።

ይህ ታላቅ ክስተት ሕፃናቱ ገና በለጋነታቸው ለዓለም ደህንነት እንዲያስቡና በውስጣቸው ሰላምን እንዲያሰርጹ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ታውቋል። በተጨማሪም መርሃ ግብሩ እያንዳንዱ ሰው ቆም ብሎ በማሰብና ለዓለም ሰላም በጎ ምኞትን በመመኘት የራሱን አሻራ ማሳረፍ እንደሚችል ትልቅ ማሳሰቢያ ሆኖ ማለፉ ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...