የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚያስገነባው ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ መገለጹ ይታወሳል።
3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ የአየር ማረፊያ ግንባታ፣ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ በአሁኑ ሰአት ለ2,500 አባወራዎች መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንና በመስከረም ወር ለማስረከብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
“አካባቢው ላይ የነበሩ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው፤ መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው፤ እንደተጠናቀቀ ወደ ተሰራላቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ይዘዋወራሉ፡፡” ብለዋል፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡
