(ሙሉውን መግለጫ ይመልከቱ )
የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመክፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብር ከፋዮችን በሚመለከት።
እንዲሁም የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ያልተወጡ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ መደረግ ስላለበት ዝርዝር ሃሳብ የያዘ ደብዳቤ በቢሮው የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ተፈርሞ ለሁሉም ለግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተልኳል።
ደብዳቤው “የተወሰኑ ግብር ከፋዬች በህጉ የተጣለባቸውን ግዴታ ለመወጣት የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ ባለው የተለየ ባህሪ ምክንያት መቸገራቸውን በተለያየ ጊዜ በመጥቀስ አቤቱታ ያቀረቡ” መሆኑን ገልጿል።
ይሁን እንጂ የግብር ሕጉ ለየትኛውም የንግድ ዘርፍ በተለየ መልኩ የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ቀሪ አለማድረጉንም አሳውቋል።
ይህንኑ ግዴታ አለመወጣትም አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የተለየ ባህሪ ያላቸው የተወሰኑ የሥራ ዘርፎች የግብር ህጉን ድንጋጌዎች በአስከበረ አግባብ የገቢ አሰበሰቡን እና የአገልግሎት አሰጣቱን ፍታሀዊነት ማዕከል ያደረገ የአሰራር ሥርዓት ለ2017 የግብር ማሳወቂያ ጊዜ ሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታን ተፈጻሚነት በቅጣት ብቻ በማለፍ ማዘግየት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብሏል።
ስለሆነም የደረጃ “ሀ” እና የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዬች የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ግብር ከፋዬች በማይወጡበት ጊዜ ለደረጃ «ሐ» ግብር ከፋዬች የወጣውን ገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 የትርፍ ሕዳግ እና በግምት ግብር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 138/2010 በቁርጥ የወጪ ሰንጠረዥ መጠቀም ዘርፉ ግዴታውን በገቢ ግብር ሕጉ መሰረት እንዳይወጣ ከተማውም ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳይሰበስብ ምክንያት ስለሚሆን ይህንኑ ክፍተት ለመዝጋት በገቢ ግብር አዋጁ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 80 መሰረት ግብር በግምት በሚሰላበት ጊዜ፦
ከግብር ከፋዮች ግንዛቤ የተለየ ድጋፍ የሚፈልጉ እና ሥራቸውም ከመንግስት ጋር በተገባ ውል ብቻ የሚያከናውኑ በማህበር የተደራጁ :-
– የትምህርት ቤቶችና የምገባ ማዕከላት መጋቢ እናቶች
– በከተማ ጽዳትና ውበት ደረቅ ቆሻሻ እና ገጸ-ምድር ማስዋብ ላይ የተሰማሩ
– ከንግድ ቢሮ ትስስር የተፈጠረላቸው የሸገር ዳቦን የሚሸጡ ማህበራት
ከመንግስት ተቋማት ጋር ያላቸውን ውልና በበጀት ዓመቱ ከአሰራቸው የመንግስት ተቋም ዓመቱን ሙሉ የተከፈላቸውን ክፍያ የሚገልጽ መረጃ ሲያመጡ መረጃን መሰረት አድርጎ በሠንጠረዥ “ሐ” መሠረት ግብሩን በማስላት ገቢው ተወስኖ እንዲሰበሰብ።
በተጨማሪም የሸገር ዳቦን የሚሸጡ በተጓዳኝ የሚከናውኑ የንግድ ስራዎች መኖራቸው በመስክ ምልከታ ተረጋግጦ በየዘርፉ የቀን ገቢ ግምት እንዲገመትላቸው ተደርጎ ግብሩ ተወስኖ እንዲሰበሰብ።
የንግድ ሥራ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሞያ ፍቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ጠበቆች ፣የኢንሹራንስ ወኪሎች ፣ኢንሹራንስ ጉዳት ገማች ግለሰቦች በሚመለከት:-
ከግብር አመቱ አጠቃላይ እንደ ገቢ 35 በመቶ እንደ ወጪ 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ “ሐ” መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።
የንግድ ሥራ ያልሆነ ገቢ ያላቸው የመኖሪያ ቤት አከራዮች ከግብር አመቱ አጠቃላይ ገቢ 35 በመቶ እንደ ወጪ 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ “ሐ” መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።
በግል ኮድ 02 እና በንግድ ኮድ 03 ተሸከርካሪ የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አጠቃላይ የኪራይ ገቢ ላይ በሠንጠረዥ “ሐ” መሠረት በመረጃ የሚወሰን በመሆኑ ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።
በህግ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች /በቴክኖሎጂ ስምሪት የሚሰጣቸውን የሜትር ታከሲዎች ጨምሮ/ የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ “ሐ” መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ መወሰኑን ይገልጻል።
የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመክፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ያልተወጡ ግብርከፋዮችን በተመለከተ:-
ይሁን እንጂ የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታ የማይወጡ ከላይ በዝርዝርከተገለጹ ዘርፎች ውጭ ያሉ ግብር ከፋዬች ግብር ለመሸሽ የሚደረግ ድርጊት መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ በግብር አወሳሰን የስራ ክፍል የግምት ግብር አወሳሰን መመሪያ 138/2010 መሰረት አድርጎ የሚወሰነው ውሳኔ ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር ከፋዮች በደረጃ ተ›› አነስተኛ የማትረፊያ ህዳግ በመከፈል ከግብር ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር መሆኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 80 መሰረት የደረጃ «ሐ›› የግብር ማስከፈያ የማትረፊያ ህዳጉ እጥፍ ተወስዶ እና በታከስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 በአንቀጽ 109 እና 110 መሰረት የታክስ ጉዳቱን 40 በመቶ እና የታክሱን እጥፍ በመቅጣት ህጉን ተፈጻሚ በማድረግ ግብርተወስኖ ቅጣቱ ምንም ሳይነሳ ገቢ እንዲሰበሰብ አሳውቃለሁ፡፡
የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 21T 33 እና 82 እንዲሁም በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 17 መሰረት የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ” የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታ አመታዊ አጠቃላይ ገቢን መሰረት አድርጎ በደረጃ “ሀ” እና በደረጃ “ለ” ግብር ከፋዬች ላይ የተጣለ ሲሆን በርካታ ግብር ከፋዬችም ይህንኑ መሰረት አድርገው ግዴታቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡
