አዲስ አበባ በመጪዎቹ ዓመታት ኮድ አንድ   ታክሲዎችን ትታ ወደ አውቶብስ የትራንስፖርት ስርዓት ልትገባ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው የከተማዋ የወደፊት የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከኮድ አንድ ታክሲዎች ይልቅ አውቶብስና ከ25 ሰው በላይ የሚጭኑ ሜትር ታክሲዎችን የሚያበረታታ ስለሆነ ከተማዋ ወደዚያው የትራንስፖርት ስርዓት ትገባለች ሲሉ ነግረውናል።

አንድ አውቶብስ የ8 ታክስዎችን ያህል ይጭናል፣ከመንገድ መጨናነቅ፣ ከተመጣጣኝ የጉዞ  ታሪፍ፣ ከነዳጅ ቁጠባና ከአየር ብክለት አንፃር አውቶብስን ጨምሮ ከ25 ሰው በላይ የሚጭኑ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ለከተማዋ ተመራጭ ነው ያሉት ኃላፊው ማህበረሰቡ ብዙሃን ትራንስፖርት የመጠቀም ልምዱን እንዲያሳድግ መክረዋል።

የትራንስፖርት ቢሮ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኃላፊው አሁን ከተማዋ ውስጥ ያሉ #ኮድ_አንድ_ታክሲዎች አብዛኛዎቹ አሮጌና የከተማዋን የታክሲ መስፈርት ስለማያሟሉ ጭምር ከትራንስፖርት ስርዓቱ መውጣታቸው ግድ ነው ብለዋል።

ኮድ አንድ ታክሲዎች ከትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ሲሆኑ ሰዎችን ከስራ ገበታ አያፈናቅልም ወይ የሚል ጥያቄ ያነሳንላቸው ኃላፊው በመንግስት ድጋፍ ኮድ አንድ ታክሲዎችን ከ25 ሰው በላይ ወደ ሚጭኑ ሜትር ታክሲዎች የማሳደግ ሥራ ይሰራል  ብለውናል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአዲሱ ገብያ መገናኛና ከመገናኛ አዲሱ ገበያ፣ ከጋርመንት መገናኛና ከመገናኛ ጋርመንት እንዲሁም ከጀሞ መገናኛና ከመገናኛ ጀሞ የሚጭኑ ታክሲዎች ክልከላ የፖሊሲና ስትራቴጂው አንድ አካል ነው ያሉት ኃላፊው በዋናነት ግን እንደ ጀሞ ጋርመንትና አዲሱ ገብያ ያሉ በከተማዋ ረጃጅም ጉዞዎች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ  ታክሲዎች መንገድ እያቆራረጡ ከጉዞ ታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ ስለነበር ነው ብለዋል።

በአዲሱ የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከ2018 ጀምሮ ከጀሞ በቄራ አድርጎ ፒያሳ የሚደርስ ፈጣን የአውቶብስ መንገድ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ከሁለት ዓመት በኋላም አዲስ አበባ ከታክሲዎች ጋር  የማይገናኝ ፈጣን የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚኖራት ከኃላፊው ሰምተናል።

ሸገርን 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...