ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን ለመምታት ዛተች

Date:

ቴህራን እስራኤል እና አሜሪካ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ በዓለም ወሳኙ የነዳጅ ዘይት መተላለፊያ በሆነው የሆሙዝ የባሕር ሰርጥን ላይ ለማለፍ በሚሞክሩ መርከቦች ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ዛተች።

አንድ ኢራን ባለሥልጣን በሆሙዝ ሰርጥ “ለማለፍ የሚሞክር ማንኛውም መርከብን በእሳት ነው የምንለኩሰው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ባለሥልጣን የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ ዋና አዛዥ አማካሪ የሆኑት ኢብራሂም ጃባሪ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው በተናገሩበት ወቅት ነው።

የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋቱን ያስጠነቀቁት ባለሥልጣኑ መርከቦች “ወደ ቀጠናው መምጣት የለባቸውም። ከባድ የሆነ ምላሽ ከእኛ ይጠብቃቸዋል” ሲሉ ዝተዋል።

ጃባሪ አሜሪካ “የቀጠናውን የነዳጅ ዘይት ተጠምተዋል” ያሉ ሲሆን ኢራን “በቀጠናው የሚገኙ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችን ታጠቃለች፤ ከቀጠናው ነዳጅ እንዲላክ አትፈቅድም” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...