ኢራን በባሕሬን እና በዮርዳኖስ የአሜሪካ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ፈፀመች

Date:

በባሕረ ሰላጤው የሚገኙት ዮርዳኖስ እና ባሕሬን በግዛታቸው ውስጥ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ገለጹ።

ኢራን ጥቃቱ የፈፀመችው የአሜሪካ ጥቃት ለሦስተኛ ቀን ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ነው።

የባሕሬን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሌሊቱን በተለያየ ሰዓት ሦስት ማስጠንቀቂያዎችን በማሰማት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ወደሚገኝ መጠለያ እንዲገቡ አስጠንቅቋል።

የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ዘብም በአገሪቷ አሜሪካ የምትገለገልበትን የተለያዩ ሥፍራዎች ዒላማ ማድረጉን ገልጿል።

አብዮታዊ ዘቡ በኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን – ኢርና – በተጋራ መግለጫው፣ በጥቃቱ በርካታ የጦር መሣሪያ መከማቻዎችን፣ የአሜሪካ ኃይሎች እና የአሜሪካ የባሕር እና አየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ራዳር የሚገኝበትን የሳተላይት ኮሚዩኒኬሽን ማዕከል ማውደሙን አስታውቋል።

የዮርዳኖስ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገባም ዮርዳኖስ ማክሰኞ ጠዋት ላይ በግዛቷ አራት ሚሳኤሎችን እንዳከሸፈች እና በጥቃቱ የደረሰ ሞትም ሆነ የንብረት ውድመት እንደሌለ ገልጿል።

አብዮታዊ ዘቡ በመግለጫው፣ በዮርዳኖስ የሚገኙ የአሜሪካ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረጉን ገልጾ፣ ለዮርዳኖስ መንግሥት ወይም ሕዝብ “ጥላቻ” እንደሌለው ገልጿል።

ከሦስት ቀናት በፊት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ አገራት የደረሱበት የተኩስ አቁም “አብቅቷል” ካሉ በኋላ ያገረሸው ጦርነት፣ የሰላም ተስፋን አመንምኗል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...