ኢራን በ40 ቀኑ ጦርነት 145 ቢ.ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል

Date:

በኢራን፣ በአሜሪካና በእስራኤል መካከል ለ40 ቀናት የተካሄደው አስከፊ ጦርነት በኢራን ላይ እጅግ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አስከትሎ አብቅቷል።

በአል አረቢያ ዘገባ መሠረት ኢራን ከ140 እስከ 145 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የኢኮኖሚ ኪሳራ የደረሰባት ሲሆን፣ በመሠረተ ልማቶችዋ ላይም ከባድ ጥፋት ተፈጽሟል። የኢራን ቀይ ጨረቃ ማኅበር ኃላፊ ፒርሁሴን ኮሊቫንድ እንደገለጹት፤ 125,630 የሚሆኑ ሲቪል ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 100,000 የመኖሪያ ቤቶች፣ 23,500 የንግድ ድርጅቶች፣ 339 የሕክምና ተቋማት (ሆስፒታሎችና ፋርማሲዎችን ጨምሮ) እንዲሁም 857 ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር እንደገለጹት፤ የኢራን ሚሳይል ማምረቻዎች፣ የባሕርና የአየር ኃይል መሠረቶች እንዲሁም የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመዋል።

ሳተላይት ካነሳቸው ምስሎች ለመረዳት እንደተቻለው፣ አራት ዋና ዋና የባሊስቲክ ሚሳይል ማምረቻ ጣቢያዎችና 29 የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ሥፍራዎች በመውደማቸው፣ ኢራን አዳዲስ ሚሳይሎችን የማምረትና የነበራትን የመከላከል ስትራቴጂ የመተግበር አቅሟ ለጊዜው ተገትቷል።

ጦርነቱ በኢራን ዋና ዋና የመሠረተ ልማት አውታሮች፣ በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ በነዳጅ ማከማቻዎችና በድልድዮች ላይ ካደረሰው ጥፋት በተጨማሪ የበርካታ ዜጎችን የሥራ ዕድል አሳጥቷል።

በአሁኑ ወቅት የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም፣ አገሪቱ ከደረሰባት ግዙፍ የኢኮኖሚና የወታደራዊ ውድመት ለማገገም ረጅም ዓመታት እንደሚፈጅባት ባለሙያዎች ይገምታሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...