ኢራን የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን አስተባበለች

Date:

ጦርነቱን ለመቋጨት ከአሜሪካ ጋር የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ንግግር መጠናቀቁን ተከትሎ ኢራን ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን የቴህራን መንግሥት አስተባበለ።

የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በስዊትዘርላንድ ከተካሄደው ድርድር ባደረጉት ንግግር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚካሄዱ ውይይቶች “ዛሬ ጭምር” ሊጀመሩ ይችላሉ ብለው ነበር።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ለአገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጠው ማብራሪያ፤ የኒውክሌር ቁጥጥርን በተመለተከተ የተገባ “አዲስ ቃል የለም” ብለዋል።

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ ሰኞ ጠዋት ላይ በስዊትዘርላንድ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ ኢራን የሚመለሱት መቼ እንደሆነ ተጠይቀዋል።

ለዚህም ምላሽ ሲሰጡ ሂደቱ “ቢያንስ በዚህ ሳምንት” እንደሚጀመር፤ ከተቆጣጣሪዎቹ ጋር የሚደረገው ንግግር ግን “ዛሬ ጭምር ሊካሄድ እንደሚችል” ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ኢራን “በዋና ዋና የጦር መሣሪያዎች ላይ ፍተሻ እንዲካሄድ ትስማማለች” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ጽፈዋል።

‘ኢርና’ ለተሰኘው ለኢራን መንግሥት የዜና ወኪል ቃለ መጠይቅ የሰጡት የቴህራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ ግን አገራቸው የኔውክሌር ተቆጣጣሪዎችን በተመለከተ “ምንም አይነት አዲስ ቃል” እንዳልገባች ተናግረዋል።

ከተባበሩት መንግሥታት ተቆጣጣሪዎች ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት የሚከናወነው “በፓርላማው እና በጠቅላይ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት በተቀመጡት ነባር አሰራሮች” መሠረት እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠም።

ኢራን የኤጀንሲው ወደ የኒውክሌር ስፍራዎች እንዳይጓዝ የከለከለችው ባለፈው ዓመት በተካሄደው የ12 በቀናት ጦርነት ወቅት እስራኤል እና አሜሪካ የኒውክሌር ጣቢያዎችን ከደበደቡ በኋላ ነው።

ይህንን ውሳኔ ተከትሎም የመንግሥታቱ ድርጅት ተቆጣጣሪ ተቋም የቀሩትን ባለሙያዎቹን ከኢራን አስወጥቷል።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...