በአዲስ አበባው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው የደረጃ ማጣሪያ ጨዋታ፣ ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አስደናቂ ብቃትን በማሳየት የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 አሸንፏል!
ይህ ድል ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ (ከ22 ዓመታት በኋላ) ለአፍሪካ ዋንጫ (CAN U-17) ማለፏን ያረጋገጠ ታሪካዊ ክስተት ነው።
ግቦቹን ዳዊት ካሳው – ቢኒያም አብርሃ – ብሩክ እይላቸው
ወጣቱ አጥቂ ዳዊት ካሳው በውድድሩ በአጠቃላይ ስምንት (8) ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል!
ኢትዮጵያ ባስተናገደችው በዚህ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ (የሴካፋ ውድድር) የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ለዋንጫ ይፋለማሉ።
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ !!!
