የህንፃዎች የቀለም ኮድ በስታንዳርዱ መሠረት እየተተገበረ እንደሆነ ተገለፀ

Date:

በኮሪደር ልማት መንገዶች ላይ የሚገኙ በስታንዳርዱ መሠረት ቀለም የቀቡ ÷አጥር ያጠሩ÷ መብራቶች የሰቀሉ ነዋሪዎች በአጠቃላይ 11.3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንዳደረጉ ሰምተናል።

የህንፃዎች የቀለም ኮድ ስታንዳርድ ከማስጠበቅ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን እየሰራሁ እገኛለሁ ብሏል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ህይወት ሳሙኤል የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የህንፃዎችን የቀለም ኮዶች ስታንዳርድ ማዘጋጀቱን ነግረዉናል።

የህንፃ ባለቤቶች ህንፃዎችን ቀለም ለመቀባት ይህንን ስታንዳርድ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸዉ ብቻ መሆኑንም ዳይሬክተሯ አያይዘዉ ገልፀዋል።

ለከተማዋ የሚስማሙ 13 አይነት ቀለማት መለየታቸዉ ከዚህ ቀደም ተነግሯል።

ይህም ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ህንጻ ከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣው የአፈጻጸም እርከን አቅጣጫ የቀለም ዲዛይኑን የሚተገብር ይሆናል።

ኮሪደር ልማት ባለፈባቸዉ አካባቢዎች ያሉ ግራ እና ቀኝ ቤቶች እድሳት የተደረገባቸዉ እና በስታንዳርዱ መሠረት ቀለም የተቀቡ መሆኑን የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ተናግረዋል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ በኮሪደር መንገዶች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች በስታንዳርዱ መሠረት ቀለም የቀቡ ÷አጥር ያጠሩ÷ መብራቶች የሰቀሉ ነዋሪዎች በአጠቃላይ 11.3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ያደረጉ መሆኑን ሰምተናል።

ከተማዋ በህንጻዎች የራሷ የሆነ ስታንዳርድ እና በቀለም የሚገለጽ ብራንድ እንዲኖራት የአረንረጓዴ ልማት የአርባን ዲዛይን ቅርጽ ይዞ እንዲለማ ማድረግ እንደሚኖርበት ባለስልጣኑ በመመሪያው አስቀምጧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...