ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ባህል ስፖርት አባል ሀገር ከመሆን አልፋ የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታ ያገኘችበት ዓመት መሆኑን የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ገልፀዋል።
የተሻለ ውጤት ለማምጣት በየደረጃው ከትምህርት ቤቶች እስከ ዓለማቀፍ መድረክ ብዙ ውጤቶች እንደተመዘገቡ የገለፁት ሚኒስትሯ፥በዓለማቀፍ ደረጃ በጃፓን ቶኪዮ በአትሌቲክስ ዘርፍ፣በናይጀሪያ ከ18 እና 20 በታች ታዳጊ ወጣቶች እና በቻይና ውሹ ተሳትፎዎችን በማድረግ የተለያዩ ዋንጫዎችን ማግኘት መቻሉን ጠቁመዋል።
ስፖርት የረዥም ጊዜ ሂደት ውጤት በመሆኑ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣት በታዳጊዎች ላይ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አመላክተዋል።
አያይዘውም ሀገራችን በቻይና ባደረገችው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በየዘርፉ ከፍ ብላ እያንሰራራች የታየችበት መድረክ እንደነበር ገልጸዋል።
