“የምንመኛትን ኢትዮጵያ ለማሳካት ትምህርት ላይ መስራት ይጠይቃል”

Date:

34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ፍትሀዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም! በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ሀገር ይገባታል የምንለው ደረጃ ላይ ለማድረስ መሰረት የሚጥል የትምህርት ስርዓትን መዘርጋት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

ትምህርትን በጥራት መስጠት ጥያቄ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በመጠቀም የተማረና ችሎታ ያለው ትውልድ ለማፍራት ትምህርትን በጥራት መስጠት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

ፍትሀዊ ትምህርት መስጠት ሌላኛው ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በመጠቆም በማህበረሰቡ ያለው የኢኮኖሚ ያለው ልዩነት በትምህርት ስርዓቱ መታየት እንደሌለበት ነው የተናገሩት።

እንዲሁም በትምህርት ስርዓቱ የሞራል መሰረት ሊረጋገጥ እንደሚገባ በማንሳት ሌብነትን የሚጠየፍና አቋራጭ መንገድን የማይከተል ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ ነው የትምህርት ሚኒስትሩ ያሳሰቡት።

የትምህርት ስርዓቱ ጠንካራ እንዲሆን  ፍትሀዊ፣ ጥራት ያለውና የሞራል መሰረት ያለው ትምህርት ስርዓት መገንባት እንደሚገባ ጠቁመው ባለፉት 4 ዓመታትም በእዚሁ ጉዳይ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ በቀረበ ሪፖርት የትምህርት ስርዓቱ የትምህርትን ጥራትን ለማረጋገጥ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ የትምህርት ቤት ምገባን ማጠናከር የሚሉት ይገኙበታል።

የመምህራንና የትምህርት አመራሩን አቅም ግንባታ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የትምህርት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ሂደት ከጊዜው ጋር የሚጓዝ ቴክኖሎጅን ያገናዘብ አካሄድ መከተል እንደሚገባ ተነስቷል።

በትምህርት ዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር እና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማሻሻል የሚያግዙ ውይይቶች  በ34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ የሚካሄዱ ይሆናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...