ኢትዮ ቴሌኮም በስድሰት ወር ውስጥ 85 ቢሊየን ብር ገቢ አገኝ

Date:

ኩባንያው ለምገነባቸው መሰረተ ልማቶች ባንኮች የሚያቀርቡት የውጭ ምንዛሪ የ ኢትዮ ቴሌኮምን ፍላጎት የሚያሟላ ሆኖ አላገኘሁትም ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ ፍላጎት  ጋር በተገናኘ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር እየተነጋገርኩ ነው ብሏል።

ከውጭ ምንዛሪ ገበያ መለዋወጥ ጋር በተገናኘ ኩባንያው የውጭ ምንዛሪ ሎስ ወይም መዛባት ከሚያጋጥማቸው መካከል አንድ መሆኑ ተሰምቷል።

ኩባንያው የውጭ ምንዛሪ ሎስ ወይም መዛባት  የ ኦፕሬሽኑ ወይም የአገልግሎት አቅራቢው ችግር ሳይሆን ከ ፖሊሲ ለውጥ ጋር የመጣ ነው ብሏል።

ኩባንያው ለዚህ ተጋላጭ ነው ፤ ይህም በፖሊሲ አውጭዎች የሚፈታ ነው መሆኑን ሰምተናል።

ይህ የተሰማው ኩባንያው የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባስረዳበት ግዜ ነው።

ለተጠናቀቀው 2025 የዲጅታል ኢትዮዽያ መሳካትም  ከፊት በመሆን በብርቱ መስራቱን አስረድቷል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ደንበኞች በባንክ አገልግሎት ፤ በዲጅታል እና በመንግስት አገልግሎት የዲጅታል መፍትሄዎችን በማቅረብ ከፍተኛ ስራ መስራቱን በማስረጃ አስረድተዋል።

የተለያዩ ግለሰቦች ድርጅቶች በ ማህበራዊ ሚዲያ ኮንተንት ይዘት በመስራት የገቢ ምንጭ የሆነላቸው በተዘረጋው መሰረተ ልማት ነው ተብሏል።

የቴሌኮም አጠቃላይ ደንበኞች ተጠቃሚ ቁጥር 87 ሚሊየን መድረሱን ፍሬህይወት ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በስድሰት ወር ውስጥ 85 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም ሰምተናል።

ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 23 ቢሊየን ብር ጭማሪ አለው ተብሏል።

በ ስድስት ወር ውስጥም  4 ሚሊየን የቴሌ ብር ደንበኞች ቁጥር መጨመሩን ሰምተናል።

አጠቃላይ የቴሌ ብር ደንበኞች ቁጥርም 58 ሚሊን ደርሷል ተብሏል።

ኩባንያው በቴሌብር በ ስድስት ወር ውስጥ ለ 4.2 ደንበኞች 8.6 ቢሊየን ብር ብድር ማግኘታቸውን አስረድቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...