ኢትዮ ቴሌኮም በ15ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ምርጥ ብራንዶች ሽልማት ላይ በሁለትዘርፎች “በቴሌኮም ዘርፍ እጅግ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ብራንድ” እና “ለማህበረሰቡ እና ለአካባቢ ጥበቃ በጎ አስተዋጽኦ ያደረገ እጅግ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ብራንድ” የተሰኙ ዕውቅናዎችን ማግኘቱን አስታወቀ።
ኢትዮ ቴሌኮም ለአራዳ በላከው መግለጫ በቀጣይ የኮኔክቲቪቲ እና የዲጂታል መፍትሄዎች ከማቅረብ ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ለማህበረሰቡ ዘላቂ እድገት እና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የብራንድ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ (Brand Africa initiative) ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ በመላው አህጉሪቱ ያሉ ምርጥ ብራንዶችን ደረጃ በማውጣት ዓመታዊ የሽልማት መርሐ ግብር በማከናወን በአፍሪካ የብራንድ ልህቀት ላይ የሚሰራ አህጉር አቀፍተቋም ነው።
