በሩሲያና  ዩክሬን የሰላም ሰነድ ላይ የሰፈሩ ቁልፍ ነጥቦች

Date:

▪️ ሁለት የተኩስ አቁም ስምምነት አማራጮች ቀርበዋል።

▪️ የመጀመሪያው አማራጭ የዩክሬን ጦር በዶንዬትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፣ በሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፣ ዛፖሮዢያ እና ሄርሶን ክልሎች ከያዟቸው የሩሲያ ግዛቶች መውጣትን ያካትታል።

▪️ ሁለተኛው አማራጭ የወታደሮች ስምሪትን ማስቆም፣ ምልመላ እና ለኪዬቭ የሚደረገውን የውጭ ወታደራዊ ዕርዳታ ማቆም፣ ወታደሮችን መበተን እና የሶስተኛ ሀገራት ወታደራዊ ተሳትፎን ማስቀረት የተመለከቱ አንቀጾችን ያካትታል።

▪️ ሰነዱ የዩክሬን ገለልተኝነትን እና ወታደራዊ ጥምረቶችን ለመቀላቀል ያላትን ውጥን መተው እንዳለባት ይገልጻል።

▪️ በዩክሬን የሌሎች ሀገራትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚከለክል አንቀጽ ተካቷል።

▪️ ዩክሬን ከኒውክሌር ነጻ መሆን እንዳለባትና የዩክሬን ሠራዊት ሊኖረው ስለሚገባ የመጨረሻ ቁጥር ያስቀምጣል።

▪️ በሩሲያ ላይ የተጣሉት የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን ማንሳት።

▪️ ክራይሚያ፣ ዶኔዬትስክ፣ ሉሃንስክ፣ ዛፖሮዥዬ እና ሄርሰን ክልሎች የሩሲያ ግዛቶች ስለመሆናቸው ዓለም አቀፍ እውቅና መስጠት።

▪️ በወታደራዊ እርምጃ ከደርሰው ጉዳት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን በጋራ ስምምነት ማንሳት።

▪️ የሩሲያኛ ተናጋሪ ሕዝብ መብቶችን እና ነጻነቶችን ማረጋገጥ፣ በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎች ላይ የተጣሉትን ገደቦች ማንሳት እና ናዚዝምን ውድቅ ማድረግ።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...