ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ለ1 ሺህ ሕፃናት ነፃ የልብ ሕክምና ለመስጠት አቀደ

Date:

ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ከነሐሴ 22 ቀን ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይና ለ1 ሺህ ሕፃናት ነፃ የልብ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል የበጎ አድራጎት ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ሆስፒታሉ ለዚህ ፕሮግራም ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልግ ገልጾ፣ ሕፃናቱ የሕክምና ዕድሉን እንዲያገኙ ሕብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ሆስፒታሉ ከተመሰረተበት ሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን የሥራ አፈጻጸም ባቀረበበት ወቅት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ79 ሺህ 300 በላይ ታካሚዎችን አስተናግዶ ከ5 ሺህ በላይ የልብ ሕክምና ሂደቶችን ማከናወኑን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 47 ስፔሻሊስቶችና ሱብ-ስፔሻሊስቶች እንዲሁም 63 አልጋዎች ያሉት ሆስፒታሉ፤ ከዚህ ቀደም የሕክምና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ 114 ሰዎች ነፃ የልብ ሕክምና መስጠቱን ገልጿል።

በተጨማሪም “ኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ” በሚል ስያሜ ባቋቋመው የበጎ አድራጎት ተቋም በኩል ከሌሎች የመንግሥት ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ለ207 ሰዎች ነፃ ሕክምና መስጠቱ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከአገር ውስጥ ባለፈ ከኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ አሜሪካ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፈረንሳይና ሕንድ የመጡ ታካሚዎችን ማስተናገዱን አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የታሰሩ የፖለቲካ ታጋዮች እንዲፈቱ ተጠየቀ

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መንግሥት በጠባብ ቀዳዳ የምታየውን የፖለቲካ ምኅዳር...