ኢንተር ሚላን ለሙኒኩ ፋይናል አልፈ !

Date:

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ባርሴሎናን 4ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲኔዝ ፣ ካልሀኖግሉ ፣ አቼርቢ እና ፍራቴሲ አስቆጥረዋል።

ለባርሴሎና ግቦችን ኤሪክ ጋርሽያ ፣ ዳኒ ኦልሞ እና ራፊንሀ ከመረብ አሳርፈዋል።

ኢንተር ሚላን በድምር ውጤት ባርሴሎናን 7ለ6 በማሸነፍ ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ኢንተር ሚላን ባለፉት ሶስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል።

አሰልጣኝ ሲሞኒ ኢንዛጊ ቡድኑን ከተረከቡ በኃላ ለሁለተኛ ጊዜ ቡድኑን በሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ አብቅተዋል።

በሙኒክ በሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ድል የሚቀናቸው ከሆነ አራተኛ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ይችላሉ።

ከ ኢንተር ሚላን በላይ ብዙ የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ላይ መድረስ የቻለው ክለብ ሪያል ማድሪድ ብቻ ነው።

የሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የፍፃሜ ጨዋታውን ከፒኤስጂ እና አርሰናል አሸናፊ ጋር ሙኒክ ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...