ኤምባሲዎችና የውጭ ባለሀብቶች በ«ፍራንኮ-ቫሉታ» ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ ቀጥተኛ ባለሀብቶች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ (በፍራንኮ-ቫሉታ) ነዳጅ እንዲያስገቡ የሚፈቅደውን አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አድርጓል።

በማዕከላዊ ገዢው እዮብ ተካልኝ ፊርማ ባለፈዉ ሳምንት የጸደቀው ይህ መመሪያ፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት በማቃለል የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፤ የሚገባው ነዳጅ ለተቋማቱ የራስ አገልግሎት ብቻ እንዲውል፣ ለንግድ እንዳይቀርብ እና በዲጂታል ሥርዓት በጥብቅ እንዲከታተል ይደነግጋል።

ባለፉት ዓመታት የነዳጅ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በብቸኝነት የማስገባት መብት የነበረው የመንግሥት ይዞታ ለሆነው ለኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነበር። ይሁን እንጂ ነዳጅ የሀገሪቱ ትልቁ የገቢ ምርት መሆኑ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት መኖሩ አቅርቦቱ ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ ቆይቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...