እጅጋየሁ ታዬ ሻምፒዮን ሆነች

Date:

በጃማይካ ኪንግስተን በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር ረጅም ርቀት ግራንድ ስላም ትራክ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በበላይነት አጠናቃለች።

14 ደቂቃ 54.88 ሰከንድ እጅጋየሁ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ጊዜ ሆኗል።

ቀደም ብላ የ3 ሺህ ሜትር ረጅም ርቀትን በተመሳሳይ በአንደኝነት ያጠናቀቀችው አትሌቷ
ያገኝችውን ነጥብ 24 በማድረስ የርቀቱ ሻምፒዮን ሆናለች።

በመሆኑም በአዲሱ ውድድር የአለም ሻምፒዮና የነሀስ ሜዳልያ ባለቤቷ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ የ100 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጽጌ ገብረሰላማ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ጽጌ በ3 ሺህ ሜትር ረጅም ርቀት በተመሳሳይ 3ኛ ሆና ማጠናቀቋ የሚታወስ ሲሆን ያገኝችውን ነጥብ 12 በማድረስ የ30 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።

ኬንያዊቷ አግነስ ኒጌቲች ደግሞ በአጠቃላይ የረጅም ርቀት ውጤት 2ኛ ወጥታለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...