የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እያካሄደው በሚገኘው መደበኛ ጉባኤው የግንባሩ ሊቀመንበር የነበሩትን አብዲራህማን ማህዲን ከስልጣናቸው አንስቷል።
ኦብነግ እያካሄደው በሚገኘው 5ኛ መደበኛ ጉባኤው ከስልጣናቸው በተነሱት አብዲራህማን ማህዲ ምትክ አዲስ መሪ ይመርጣል ተብሎም ይጠበቃል።
የግንባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቀድሞውን የግንባሩን ሊቀመንበር ከስልጣን በማገድ በጊዜያዊነት አብዲከሪም ሼህ ሙሴን ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ መሰየሙ ይታወሳል።
