ከሰሞኑ እስራኤል ሶስት ጋዜጠኞችና ሶስት የተረድኦ ድረጅት ሰራተኞች መግደሏ የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ

Date:

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበርያ ኤጀንሲ (ኦቻ) መረጃ መሰረት ከገባ ዘጠኝ ቀናት ብቻ ባስቆጠረው የኤፕሪል ወር እስራኤል አንድ የኤምኤስኤፍ አባልና ሁለት የፍሊስጤም ቀን ጨረቃ ማህበር ሰራተኞችን መግደሏን ገልፆል።

ይህም ከጥቅምት ሰባቱ ጥቃት ወዲህ እስራኤል በጋዛ ላይ በፈፀመቻቸው የተለያየ መልክ ያላቸው ጥቃቶች የተገደሉት የተራድኦ ድርጅት ሰራተኞች ቁጥር 412 አድርሶታል።

ኦቻ አክሎም ሶስት ፍልስጤማውያን ጋዜጠኞችም ባለፈው አንድ ሳምንት መገደላቸውን ያስታወቀ ሲሆን ኤፕሪል 6ና 7 በካንዮንስ በተፈፀሙ ሁለት ጥቃቶች አንዲት ኢስላም ማክዳድ የተሰኘች እንስት ፍሊስጤማዊ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሶስቱ ጋዜጠኞች ተገድለዋል። የጋዜጠኞቹን ህይወት በቀጠፉት ጥቃቶች ሴቶችና ህፃናት የሚገኙባቸው በርካታ ሰላማውያን ሰዎች መገደላቸውም ተዘግቧል።

የነዚህ ሶስት የሚድያ ሰዎች ግድያ ደግሞ በአጠቃላይ በእስራኤል ጥቃት በጋዛ የተገደሉት ጋዜጠኞች ቁጥር 208 አድርሶታል ተብሏል።

በሚሊዮን ሙ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...