ረቡዕ ዕለት ከታየው ትንሽ የዋጋ ጭማሪ ውጭ፣ ሁለቱ ሀገራት ጦርነቱን ለማቆም እና ቁልፍ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ የባህር ትራንስፖርት መስመርን መልሶ ለመክፈት የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ከታወቀ ወዲህ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ መጥቷል።
የአለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ሳምንቱን ሲጀምር በአንድ በርሜል በ86.80 ዶላር አካባቢ ይገበያይ የነበር ሲሆን፤ ከስምምነቱ በኋላ የ2 በመቶ ያህል ቅናሽ በማሳየት በ74.80 ዶላር እየተገበያየ ይገኛል።
