ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው

Date:

በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ መካተቱ ታውቋል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ (ለምሳሌ ከዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ እና ሌሎችም መድረኮች) ፣ በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች እንደሚሁም ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣ ከስፖንሰርሺፕ እና ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው “ሌሎች ገቢዎች” በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣኑ የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...