የግብይትና የታክስ ህጎችን ባላከበሩ 11 ሺህ 283 ነጋዴዎች ርምጃ ተወስዷል

Date:

3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫን አቅርበዋል።

ከንቲባዋ ገቢና ወጪን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ በ2017 በጀት ዓመት ከ233 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል።

የተሰበሰበው ገቢም ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ83.3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ የሌብነትና ብልሹ አሰራር በፈጸመው 247 ሰራተኞች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 11 ወራት የግብይትና የታክስ ህጎችን በላከበሩ እና ደረሰኝ ባልሰጡ 11 ሺህ 283 ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱንም አመላክተዋል።

በጋዜጣ_ፕላስ |

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...

አሜሪካ እና እስራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለአገሪቱ ጦር የማስረከብ ዕቅድ

አሜሪካ ድጋፏን በሰጠችው ዕቅድ መሠረት እስራኤል እና ሊባኖስ፤ የደቡብ...

የመሬት ልማትና አስተዳደር በበጀት ዓመቱ 63 በመቶ ያህሉን ማሳካት አልቻለም

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሊገባደድ በተቃረበው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ...