ከ100 ሺህ ቶን በላይ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋለ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

Date:

በአዲስ አበባ በዓመት ከመነጨው 100 ሺህ 585 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።

በከተማዋ 325 የመልሶ መጠቀም ማህበራት የተቋቋሙ ሲሆን በዓመት ከተመረተው 983ሺህ 944 ቶን ቆሻሻ 100 ሺህ 585 ቶኑን መልሰው ጥቅም ላይ ማዋላቸውን አስታውቀዋል።

አምስት ሺህ 460 ቶን ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ስራ ማዋል ተችሏል ብለዋል።

በጽዳት ዘመቻ 675 ሺህ 384 ነዋሪዎችና ሁለት ሺህ 540 ተቋማት በሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተሳትፈዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ በተሰራው የጽዳት ስራ በከተማዋ የሚከሰቱ የወረርሽኝ ምጣኔዎችን መቀነስ፣ ወንዟችና አካባቢን ከብክለት መታደግ፣ ቆሻሻን ወደሀብት መቀየር እና ከተማዋን ውብና ጽዱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ቆሻሻን ከመሰብሰብ ባለፈ በአግባቡ የማስተዳደርና መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

(ኢፕድ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...