አሃዱ ባንክ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ

Date:

አሃዱ ባንክ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማስመዝገብን ያስታወቀ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ወይም የ90.9 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ ትርፍ የእርጅና ቅናሽ እና ተያያዥ ወጪዎችን ጨምሮ፣ ለመጠባበቂያ ከተቀመጠው እና ከግብር በፊት 569 ሚሊዮን ብር ማትረፉን በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው ትርፍ በ450 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን፣ የ278.1 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 7.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ68 በመቶ ዕድገት በማሳየቱና በውጭ ምንዛሪ ገቢ ረገድም ከ88 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል።

የደንበኞች ቁጥር 1.1 ሚሊዮን መድረሱን የገለፀው ባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ የ57 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን አስታውቋልአስታውቋል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...