ከ100 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው

Date:

በተያዘው ክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ100 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ ሕክምና አገልግሎት የመስጠት ሥራውን በዛሬው እለት መጀመሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜድካል ኮሌጅ አስታውቋል፡፡

የሜዲካል ኮሌጁ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ጀማል ሺፋ፤ “የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ ሁሌም የሚሰራ ቢሆንም በዚህ ዓመት ከሐምሌ 21 እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ብቻ በሚሰጠው የነጻ ምርመራ 100 ሺሕ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል” ብለዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ከ94 ሺሕ ለሚበልጡ ሰዎች የነጻ ሕክምና አገልግሎት እንደተሰጠ አስታውሰው፤ የዘንድሮውን መርሃ-ግብር “በጎ ፈቃደኝነት ለጤናማ ማኅበረሰብ” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

ነጻ ምርመራው በተለይ የካንሰር፣ የጎሮሮ፣ የዓይን እና መሰል ትላልቅ የበሽታ አይነቶችን የነጻ ምርመራ እንደሚያደርጉ ከ50 በላይ የሕክምና መሳሪያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በምርመራ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ለአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ደም መለሰገስ፣ እና ሌሎችም የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ መሳተፍን እንደሚጨምር ተነግሯል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...