‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ”

Date:

መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት።
ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡

ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡

ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።

ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት፤ ‹‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል›› አለኝ፡፡

‹‹እንዴት?›› ብለው ‹‹አላየህም ሲያጨበጭብ?›› አለኝ፡፡

‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል›› አልኩት፡፡

‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡”

አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት ሙሴ ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ/ም

(Yared Shumete)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...