ከ180 በላይ የሲቪል ማኅበራት 34ቱ የመራጮች ትምህርት ሊጀምሩ ነው

Date:

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ለማበረታታት፣ ከ180 በላይ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች የመራጮች ትምህርት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አስታውቋል።

ድርጅቶቹ ፈቃዱን የወሰዱት በሁሉም ምርጫ የሚካሔድባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ተሰማርተው መራጮችን የማንቃት እና መብታቸውን እንዲጠቀሙ የማበረታታት ትምህርት እንዲሰጡና ሂደቱን እንዲታዘቡ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሁሴን፡ “ፈቃድ ከወሰዱት ድርጅቶች መካከል 34ቱ የፋይናንስ ድጋፍ አግኝተው ወደ ማስተማር ሥራ የሚያስገባቸውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ናቸው” ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ የአማራ ክልል የሲቪል ማኅበራት ሕብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ደስታ የመራጮች ትምህርት እንዳይሰሩ የተለያዩ ተግዳሮቶች እንደገጠሟቸው ተናግረዋል።

“ሕብረቱ በምርጫ ቦርድ መመሪያ መሠረት እየሠራ ቢሆንም፣ የፋይናንስ እጥረት እና በአንዳንድ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ስጋት መራጮችን የማስተማር ስራውን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እንቅፋት ፈጥሯል” ሲሉ  አብራርተዋል።

ምክር ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆንና የዜጎች የመምረጥ መብት እንዲረጋገጥ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...