በንግድ ቢሮዉ ከተተመነዉ 70 ግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ ከ72 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን የሚደረገዉ ቁጥጥር እንደሚቀጥል ገልጿል ፡
እርምጃ ከተወሰደባቸዉ 72 ዳቦ ቤቶች ዉስጥ 65ቱ ዳቦ ቤቶች ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ መደረጉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የህጋዊ ስነ ልክ ቡድን መሪ ደረጀ በቀለ ለጣቢያችን ተናግረዋል ፡፡
ዳቦ ከመሰረታዊ ድጎሞ ሸቀጦች ዉጭ መሆኑን ያስታወሱት የህጋዊ ስነ ልክ ቡድን መሪዉ ንግድ ቢሮዉ ዳቦ ቤቶች በተለጠፈዉ ዋጋ እና ግራም እየሸጡ ነዉ የሚለዉን ብቻ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ንግድ ቢሮዉ በክትትል እና በቁጥጥር ወቅት ከለጠፉት የዳቦ መሸጫ ዋጋ በላይ እና ከተተመነዉ ግራም በታች መጠን ያለዉ ምርት በሚሸጡ ዳቦ ቤቶች ላይ ከፅሁፍ እስከ ንግድ ፍቃድ መሰረዝ እርምጃ የሚወስድበት አሰራር ስለመኖሩአቶ ደረጀ በቀለ አስታዉቀዋል ፡፡
ዳቦ ቤቶች ከለጠፉት ከዋጋ ዝርዝር በላይ ሲሸጡ እንዲሁም ግራም አጉድለዉ ሲገኙ ህብረተሰቡ በነፃ ስልክ ቁጥር 85 88 ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ተነግሯል፡፡
