“ወደ ኔቶ መቀላቀል ይችላሉ ብዬ አላስብም”፦ ትራምፕ ከታይም መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ዩክሬን የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
◾️ክሬሚያ በዩክሬን የሰላም ስምምነት መሠረት “የሩሲያ ግዛት ሆና ትቀጥላለች”፤ ዘለንስኪም ይህን ይረዳል፡፡
◾️የግጭቱ መነሻ የዩክሬን የኔቶ አባልነት ውይይት በመሆኑ ኪዬቭ ግጭቱን በማስነሳት ተጠያቂ ናት፡፡
◾️በዩክሬን ዙሪያ የሚደረገው ድርድር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፤ ስምምነቱ “በጣም ተቃርቧል”፡፡
◾️በፕሬዝዳትነታቸው ጊዜ በዩክሬን ሰላም እንደሚመጣ ያምናሉ፡፡
◾️ግጭቱን በአንድ ቀን ውስጥ ማቆም እችላለሁ የሚለው ንግግራቸው ማጋነን እና ምሳሌያዊ አነጋገር እንደሆነ አምነው፤ ግጭቱን ለማቆም ቃል ገብተዋል፡፡
◾️በዩክሬን ያለው ግጭት ለረጅም ጊዜ አይቀጥልም ብለዋል፡፡
◾️በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል ስምምነት ከተደረሰ አሜሪካ ከዩክሬን እና ሩሲያ ጋር የንግድ ግንኙነት ማድረግ የምትችልበትን ሁኔታ ትገመግማለች።
