ፍላይ አዲስ ዛሬ ይብረሩ ነገ ይክፈሉ በሚል መርህ ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚሄዱ ዜጎች ለጉዞና ለማማከር አገልግሎቶች የዱቤ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምነት ማድረጉን አስታውቋል
ድርጅቱ ከዚህም ጋር በተያያዘ በአሁን ሰዓት እነዚህን የጉዞና የማማከር አገልግሎቶችን ይበልጥ በማዘመንና በማስፋት ከአውሮፓ፣ ፖላንድ፣ ቱርክ፣ ጣሊያን፣ ካናዳ፣ ሩሲያ ሀገራት በተጨማሪ በሌሎች ሀገራትም ዜጐች አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር የዱቤ አገልግሎት በመስጠት ሕብረተሰቡ በሚሄዱባቸው ሀገራት ሁሉ ለሚያስፈልጓቸው የጉዞና ሌሎች አገልግሎቶቹን በዱቤ ማግኘት እንዲችሉ ከባንኩ ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል
ደንበኞች የዱቤ አገልግሎቱን ለማግኘት በዳሽን ባንክ ሱፐር አፕ ላይ በሚያንቀሳቅሱት የገንዘብ መጠንና በሰው ዋስ እንደሆነ ተገልጿል
ዳሽን ባንክ ከድርጅቱ ጋር አጋር በመሆን የዱቤ አገልግሎት ሲሰጥ ማለትም ትኬት፣ የሆቴል፣ የኢንሹራንስ፣ ቪዛና መሰል ለጉዞ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ክፍያ በዳሽን ባንክ በኩል እንዲከፍሉና ክፍያውን እንዲፈፅሙ የዱቤ አገልግሎቱን በየወሩ የሚፈፀም ሲሆን ደንበኛው ማስያዣና ሌሎች ዶክመንቶች አቅርቦ ለጉዞ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ይሟሉላቸዋል፡፡ ለሕክምና፣ ለትምህርት፣ ለሥራ፣ የሽርሽር ጉዞ ለሚያደርጉት ጉዞ ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን የዱቤ አገልግሎት በመስጠት እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
ፍላይ አዲስ ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት ሕጋዊ እውቅና በማግኘት ላለፉት አራት ዓመታት አውሮፓ፣ ፖላንድ፣ ቱርክ፣ ጣሊያን፣ ካናዳ፣ ሩሲያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ለትምህርት፣ ለሥራና ለሕክምና እንዲሁም ለጉብኝት ጉዞ ለሚያደርጉ ዜጎች ሕጋዊ የጉዞና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
