“ወጣቱን በጉልበት እያፈሱ ወደ ጦርነት እየነዱት ነው!”

Date:

“ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት በትግራይ፦ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበረሰብ አንቂዎች ሚና” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የትግራይን ሕዝብ ለዳግም ስቃይ፣ ጥፋትና የሕልውና አደጋ ለመዳረግ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ በብርቱ አውግዘዋል።

ቡድኑ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ በአቋራጭ ሥልጣን ለመያዝና ወንጀሉን ለመሸሸግ ወጣቶችን ከትምህርት ገበታ፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከመንገድ በጉልበት እያፈሰ ወደ ጦርነት እንዲገቡ በማድረግ እንደ ካርድና መያዣ እየተጠቀመባቸው መሆኑን በማንሳት ይህ ሰብዓዊነት የጎደለው እኩይ ድርጊት መቆም እንዳለበት አሳስበዋል።

ሴንተር ፎር ሪስፖንሲቢል ኤንድ ፒስፉል ፖሊቲክስ (CRPP) ከትግራይ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ ምሁራን፣ የማኅበረሰብ አንቂዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የመደበኛና የዲጂታል ሚዲያ ሚናን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዕለቱም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ መገናኛ ብዙኃን ሕጋዊ ሰውነትን በመላበስ የትግራይን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ መሠረት ያደረጉ ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

ላለፉት 5 አስቸጋሪና ፈታኝ ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም)...

ንባብ ለሕይወት  እየመጣ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

ለኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች እስከ 250 ሺህ ዶላር ዋስትና

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመሰማራት በሚፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ...