አቢሲኒያ የበረራ አገልግሎትና የአቪዬሽን አካዳሚ የመጀመሪያውን የሕዳሴ ግድብ የጎብኚዎች ቻርተር በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡
አቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት ወደ ሕዳሴ ግድብ ያስጀመረው በረራ፣ ስፍራውን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ በማደረግ ረገድ አዲስ ምዕራፍ ነው ተብሏል።
የግድቡን ምርቃት ተከትሎ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካውያን የዲያስፖራ ጎብኚዎችን የጫነው የአቢሲኒያ አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ወደ ስፍራው መብረሩ ተነግሯል፡፡
ኩባንያው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ “ጎብኚዎችን ወደዚህ እውነተኛ የሀገር ኩራት የሆነ ታሪካዊ ሥፍራ በማድረስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቻርተር አየር መንገድ በመሆናችን ታላቅ ክብር ይሰማናል።” ብሏል፡፡
