የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ

Date:

አርብ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ለታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ እና ለአካባቢዋ ማህበረሰብ ትልቅ የምስራች የሆነው የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ፕሮጀክቱ ለረጅም ዓመታት በዕቅድና አተገባበር መጓተት ቢፈታተነውም፣ በመደመር እሳቤ የታዩትን የአፈጻጸም ችግሮች በመፍታትና በጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ወደ ታላቅ በረከት መለወጥ ተችሏል ነው የተባለው።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ጥቅሞችና አቅም፡-

የውሃ መያዝ አቅም፡ ግድቡ 185 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በመስኖ የማልማት ዕድል ይፈጥራል።

አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ፡ በአካባቢው የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪዎች የልማት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ ያስችላል።

የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፡ ለጎንደር ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ አቅራቢያ ከተሞች አስተማማኝ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ያቀርባል።

ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ፡-

ከግድቡ መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ በሰው-ሰራሽ ሀይቁ ዙሪያ የሚስፋፉት የከተማ ግብርና፣ መጠነ-ሰፊ የአሳ እርባታ፣ እንዲሁም ለቱሪዝም ልማት የሚሆኑ የመዝናኛ ሪዞርቶች እና ሎጆች ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥሩና ንግዱን የሚያነቃቁ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ጎንደር ገና ብዙ ሊሰራላት የሚገባ ከተማ በመሆኗ ህዝቡ በልማት ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ እድገት ሁሉንም አካባቢዎች ያካተተና ሁሉንም ዜጋ እኩል የሚያቅፍ እንዲሆን የማስፋፋትና የመደገፍ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...