ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ አሁን ከምንገኝበት ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ የአዋጁን ድንጋጌዎች በማሻሻል የታክስ ሥርዓቱ መሠረታዊ የታክስ መርሆዎችን ለማሳካት በሚያስችል መልኩ እንዲቀረጽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የማሻሻያ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በማሻሻያ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
(የገቢዎች ሚኒስቴር)
