የኢራን ሚሳኤሎች በአውሮፓ አህጉር መድረስና ማጥቃት የሚችሉ ናቸው ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናት አስጠንቅቀዋል፡፡
አንድ የእስራኤል ወታደራዊ ባለስልጣን በሰጡት ማብራሪያ የኢራን ባለስቲክ ሚሳኤሎች በእስራኤልና በየትኛውም የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ያሉ ኢላማዎችን መምታት የሚያስችል ብቃት አላቸው ነው ያሉት፡፡
ኢራን የዚን አይነቶቹን የረጂም እርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎቿ ቁጥርም ለአሁኑ ከአራት መቶ አይበልጥም እንጂ የውጤት እርቀቱ ግን ከሁለት ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ነውና ከእስራኤል ባለፈም የአውሮፓን ሀገራት ለማጥቃት ይችላሉ ነው የተባለው ፡፡
ይሁንና እስራኤል በድንገተኛ ጥቃት እነዚህን የኢራን የረጅም እርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች በማውደም ቁጥራቸውን መቀነሷን የዩኒት ኒውስ ዘገባ ያብራራል፡፡
