“የሚዲያ ነፃነትን የሚገድቡ የሕግ ማዕቀፎች ተወግደዋል” — አቶ አደም ፋራህ

Date:

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፤ መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችል ምቹ አውድ ለመፍጠር መንግሥት በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ገለጹ።

አቶ አደም በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተገኝተው የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴና የማሻሻያ ተግባራት በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት፤ በተለይም ከለውጡ ወዲህ ሚዲያዎች የለውጡ አካል ሆነው እንዲሻሻሉ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷል።

ኃላፊው አክለውም ቀደም ሲል መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዳይሰሩ እንቅፋት ሆነው የቆዩ የሕግ ማዕቀፎች እንዲሻሻሉ መደረጉን ጠቁመዋል። ይህም የሚዲያ ተቋማት ያለምንም ገደብ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል አዲስ የሥራ ከባቢ መፍጠሩን ገልጸዋል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንም ይሄንን የተገኘውን የሚዲያ ነፃነት በአግባቡ በመጠቀም በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ እያሳረፈ እንደሚገኝ አቶ አደም አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ተቋሙ የዘመኑን የመገናኛ ብዙሃን ውድድር ሊቋቋም በሚችል መልኩ ራሱን በዘመናዊ መሣሪያዎችና ምቹ የሥራ አካባቢ መገንባቱን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ፋና ሚዲያ ዘመናዊነትን ከሕዝብ አመኔታ ጋር አቀናጅቶ መጓዙ ተልዕኮውን ይበልጥ እንዲወጣ እንደረዳው ጠቅሰው፤ ተቋሙ አሁን ባለው ጠንካራ ቁመና ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ እያላቀ እንደሚሄድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...