አዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ የሥራ ፈቃዱ በመሰረዙ ምላሽ ሰጠ

Date:

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የ”አዲስ ስታንዳርድ” የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ምስክር ወረቀትን ሰርዟል። ሚዲያው እውቅናውን ተነፍጓል የስራ ፍቃዱን ተነጥቋል።

ባለስልጣኑ ሚዲያው የሀገርንና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ በማሰራጨቱ እና በተሰጠው ምክርና ማስጠንቀቂያ ባለመታረሙ መሆኑን ገልጿል።

የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገዋል።

” እስካሁን ምንም ዓይነት መደበኛ ማስጠንቀቂያ አልደረሰንም ” በማለት ” ክሱ ከእውነት የራቀ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ‘ አዲስ ስታንዳርድ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ደርሰውታል ‘ የሚለው ክስ ከእውነት የራቀ ነው። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ቀደም ሲል ስለነበሩ የሕግ ጥሰቶችም ሆነ ስለተወሰዱ እርምጃዎች ለአዲስ ስታንዳርድ የዜና ክፍል በይፋ ያሳወቀው ነገር የለም ” ብለዋል።

አሳታሚው ጃኬን ፐብሊሺንግ መብቱን ለማስከበር የሕግ አማራጮችን እየተመለከተ መሆኑን አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...