የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም በዓል በየዓመቱ ለምን ሚያዚያ ፳፯ ቀን ይከበራል?

Date:

ዓመታዊ በዓሉ ሚያዚያ 27 በደመቀ ሁኔታ የሚከበርበት ምክኒያት 5 ናቸው።

፩. ጃንሆይ በለንደን ባት በተባለ ቦታ ላይ በነበሩበት ወቅት ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው በሚያዚያ ፳፯ ነው።

፪. በአዲስ አበባ የነጻነት የድል በዓል መከበር የጀመረው በ፲፱፻፴፫ ሚያዚያ ፳፯ በመሆኑ

፫. ታቦቱ ከጃንሆይ ጋር ወደ ኢትዮጲያ በመጣ ጊዜ በቤተ መንግስታቸው ፪ ዓመት ካቆዩ በኋላ የቀድሞ ቤተ ሳይዳ ሆስፒታል የአሁኑ የካቲት ፲፪ ሆስፒታል ላይ ቤተክርስቲያን ካለቀ በኋላ ታቦቱ ወደ መቅደሱ የገባው ፲፱፻፴፭ ዓ.ም ሚያዚያ ፳፯ ነው።

፭. አሁን ያለበት ከተፈሪ መኮነን አጠገብ የሚገኘው ቤተክርስቲያን የመሠረቱ ድንጋይ የተጣለበት ፲፱፻፵ ዓመተ ምሕረት ሚያዚያ ፳፯ ነው።

5,በ፲፱፻፵፪ ዓመተ ምሕረት ታቦተ ሕጉ ወደ መቅደሱ የገባበት ሚያዚያ ፳፯ በመሆን በዓሉ በዚህ ቀን ይከበራል።

የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ታቦቱ ወጥቶ መከበር የጀመረው በ19 82 ዓ.ም ሲሆን የአካባቢው ምዕመናን ባቀረቡት ጥያቄ መመረት በዓመት ፩ ጊዜ እንኳን ታቦቱ ወጥቶ ቢባርከን በማለት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በጊዜው በነበሩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ፈቃድ የሚወጣበትንም ዕለት ምክኒያቱ ተናግረው ሚያዚያ 27 እንዲወጣ ተደርጓል ።

©የገዳሙ ሚዲያ

እንኳን ለ፸፭ኛ ዓመት የቅዳሴ ቤት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ተጨማሪ መረጃ

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ታቦት ሦስት ስያሜዎች

1ኛ.ዴር ሱልጣን ይባላል ዴር ሱልጣን ማለት የንጉሥ ገዳም ማለት ነው እኛ ኢትዮጲያዊያን በኢየሩሳሌም ገዳማቶች እንዳሉን ይታወቃል የዛሬ 119 ዓመት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ይህንን ታቦት የላኩት በዴር ሱልጣን ገዳም ሁኖ በዛ ላሉ ምዕመናን መጸለያ፣መማፀኛ እንዲሆን ብለው ነው።

2ኛ.ስደተኛው መድኃኔዓለም ነው ይህም የተባለበት በእንግሊዝ ሀገር በስደት ከጃንሆይ ጋር 4 ዓመታትን ቆይቷል በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን ከዛም እንግሊዝ ባት በምትባል ቦታ ከዛም ወደ ሱዳን ካርቱም ከዛም አዲስ አበባ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የአሁኑ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀጥሎ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል ቤተ ሳይዳ በአሁኑ ስሙ የካቲት 12 ሆስፒታል ውስጥ በመጨረሻም አሁን ያለበት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ስደተኛው ተብሏል ።

3ኛ.ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ማለት ያዘኑት የምስኪናን ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ ማለት ነው።

©ምስካየ ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ክፍሌ አቦቸር እና ‹‹ይህ ነው ምኞቴ…››

ሠሎሞን ለማ ገመቹ ግዮን መጽሔት :- ሻለቃ ከፍሌ አቦቸር ስለ...

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...