የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ባልተጠበቀ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

Date:

​የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸው የመጀመሪያ ማቆሚያ ባደረጓት አዲስ አበባ ሰኞ ምሽት ገብተዋል።

ይፋ ባልተደረገው በዚህ ጉብኝት ላቭሮቭ ማክሰኞ ዕለት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና ከሌሎች ከፍተኛ መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​የሩሲያ መንግስት ሚዲያ (አርአይኤ) እንደዘገበው፣ በምክክሩ ወቅት ትኩረት ከሚሰጣቸው ዋነኛ ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፍ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ መገንባት የሚለው ይገኝበታል።

​በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ንግድ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ይመክራሉ።

ሰርጌ ላቭሮቭ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ከፈረንጆቹ 2022 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ቀጥሎ ወደ የትኞቹ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚጓዙ ግን እስካሁን በይፋ አልተገለጸም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እናት ፓርቲ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን “የእነ አጼ በጉልበቱ መፈንጫ” ሲል ኮነነ ውጤቱንም እንደማይቀበል አስታወቀ

እናት ፓርቲ በቅርቡ የተካሄደውን የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ አጠቃላይ ሂደትና...

የምክክር ኮሚሽኑ መዝጊያ

የኦሮሚያ ክልል ያቃረበውን ቅሬታ የተመለከተው የአሸማጋይ ቡድን አዲስ አበባ...

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...