የሮይተርስ የዜና ወኪሎች በኢትዮጵያ ታገዱ

Date:

ኢትዮጵያ የሮይተርስ የዜና ወኪል ጋዜጠኞችን በሀገሪቱ የመሥራት መብት እንደነጠቀች የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ የሚካሔደውን 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለሮውተርስ የተሰጠው ፈቃድ እንደተሰረዘ የዜና ወኪሉ ቃል አቀባይ በኢሜይል እንደገለጹ ዘገባው ይጠቁማል።

ከዚህ በተጨማሪ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ሦስት የሬውተርስ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የመዘገብ ፈቃድ እንዳልታደሰ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ሬውተርስ የውሳኔው ገፊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ያለው ነገር የለም። ሁሉም ጋዜጠኞች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሮውተርስ ስለ ኢትዮጵያ በሚሠራቸው ዘገባዎች የጀርባ አጥንት እንደነበሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ገልጿል።

ሬውተርስ “ጉዳዩን እየገመገመ” እንደሚገኝ እና “ነጻ፣ ገለልተኛ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ” ስለ ኢትዮጵያ ዘገባዎች መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዳላገኘ በዘገባው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባልደረባ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። 

ሬውተርስ ከጥቂት ቀናት በፊት ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ማሰልጠኛ መከፈቱን የሚዘግብ ሰፊ ሪፖርት አቅርቦ ነበር ሲል ዶቼቬሌ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...