አዲሱ የሱዳን መንግሥት መቼ እንደሚመሰረት አልታወቀም
በሱዳን መንግሥት ጦር ኃይል አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን የተሾሙት ካሚል ኢድሪስ፣ ከ2013 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ወዲህ የሱዳን የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ባለፈው ቅዳሜ ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን፤ ጠ/ሚኒስትሩ ጊዜያዊ መንግሥቱን በትነዋል ሲሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ባደረጉት ንግግር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ገለልተኛ ሆነው እንደሚቀጥሉና መረጋጋትን፣ ደህንነትንና ሱዳንን መልሶ ለመገንባት ትኩረት እንደሚያደርጉ ካሚል ኢድሪስ ቃል ገብተዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከአጋር ፓርቲዎች ጋር ትይዩ መንግሥት ለመመሥረት ማቀዱን ማስታወቁን ስፑትኒክ በዘገባው አስታውሷል፡፡
