የሲዳማ የዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል ይከበራል

Date:

የሲዳማ ተወላጆች በእነዚህ ቀናት ቂም ቁርሾን ሽረው፣ በእርቅ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲስ ዓመት ይሸጋገራሉ።

ለዚህ ተምሳሌትነትም በየደጃፋቸው በእርጥብ እንጨት ባዘጋጁት “ሁሉቃ” በኩል የማለፍ ሥነ ሥርዓት ይፈጽማሉ።

ቤተሰብ በአንድ ላይ በመሰባሰብ በጋራ ማዕድ ይቋደሳል፤ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲስ ዓመት ያሸጋገራቸውን ፈጣሪውንም ያመሰግናል።

በጫምባላላ በዓል የብሔሩ ተወላጆች የባህል ልብሳቸውን ለብሰው ወደ “ጉዱማሌ” አደባባይ በመውጣት፣ በ”ቄጣላ” ባህላዊ ጭፈራ እና በባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች በጋራ ያከብራሉ።

በኮሪደር ልማት በአዲስ መልኩ የተሞሸረችው ውቢቷ የሐዋሳ ከተማም ይህን ትዕይንት ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች።

ሐዋሳን እንዲጎበኙ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግብዣ የቀረበላቸው ኢትዮጵያውያንን እና በርካታ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶችም በዚህ ትዕይንት ላይ እንደሚታደሙ ይጠበቃል።

ፊቼ ጫምባላላ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ከ10 ዓመት በፊት መመዝገቡ የሚታወስ ነው።

እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ በዓል አደረሳችሁ! – “አይዴ ጫምባላላ!”

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...