የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ታዬ ደንደአ  የመከላከያ ምስክሮች  አለመቅረባቸው ተገለጸ

Date:

ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት፣ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ሕጉን በመተላለፍ በሚሉ ተደራራቢ ወንጀሎች ተከሰው የፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዴዔታ ታዬ ደንደአ  የመከላከያ ምስክሮች ዛሬም በችሎት አለመቅረባቸው ተገልጿል።

አቶ ታዬ ደንደአ ከአንድ ዓመት የእስር ቆይታ በኋላ በዋስ ተለቀው ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት በነበረው ችሎት ላይ አምስት የመከላከያ ምስክሮች የምስክር ቃላቸውን እንዲያሰሙ ጠይቀው ነበር።

በዚህም መሠረት ሕዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ማለትም፤ የፖሊስ ኮሚሽነር መላኩ ፈንታና አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ለፍርድ ቤቱ በፅሁፍ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ቀሪዎቹ ሦስት የመከላከያ ምስክሮች በሁለተኛው የችሎት ውሎ የመከላከያ ምስክርነታቸውን ለመስጠት ያልተገኙ ሲሆን፤ በዛሬው ቀጠሮም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ጸረ ሽብር ወንጀል ችሎት ሳይቀርቡ መቅረታቸውን አሐዱ በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል፡፡

በዚህም ቀሪዎቹ ሦስት የመከላከያ ምስክሮች ባለመቅረባቸው ምክንያት፤ ለቀጣይ ሰኔ 30 መዝገቡ ተቀጥሯል።

የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ  በችሎቱ በሰጡት ቃል፤ “ለምን ፍርድ ቤት የያዘውን የምስክር መጥሪያ ተቀብለው መልስ እንዲሰጡ አይሆንም? ተጨማሪ ቀጠሮም መሰጠት አይገባም” ብለዋል።

የአቶ ታዬ ጠበቃ በበኩላቸው “ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ በአግባብ መድረስና አለመድረሱን መልስ ሊሰጠን ይገባል”  ያሉ ሲሆን፤ በአካልም ባይሆን በጹሁፍም ማቅረብ እንዲችሉ ችሎቱ ሊያሳስብ ይገባል” ብለዋል።

እንዲሁም መጥሪያው የሚደርስበትን መንገድ በማሰብ እንደሚገባና መጥሪያ አንቀበልም የሚሉ ምስክሮችም ካሉ ችሎቱ ሊቀበልው ይገባልም ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም መጥሪያው በፌደራል ፖሊስ በኩል እንዲደርስ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ችሎቱ መጥሪያው እንዲደርስ እና ተከላካይ ምስክሮች መልስ እንድሰጡ  በፌደራል ፖሊስ እንዲደርሳቸው ትእዛዝ በመስጠት፤ የመዝገቡን ምስክር ለመስማት  ለሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል።

በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...